Partnership Form

የንሥር  ኢንተርናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ትልቅ ሀሳብ አለወት? ንሥር ብሮድካስት ለህብረተሰባችን የሚዲያ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። የተቋማችን አጋር መሆን ይፈልጋሉ? ከሆነ፣ የአጋርነት ስምምነት ቅጽ በመሙላት የንሥር ብሮድካስት አጋር ይሁኑ። ትብብር፤ የልምድ ልውውጥለተሻለ የህዝብ አገልግሎት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።
ይህ የአጋርነት ማመልከቻ ፎርም በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበርና አቅምን ለማሳደግ የሚያስችልና በፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስምምነት ነው። በአጋርነቱ የጋራ ትብብር እንጂ የጋራ ሃብት አይኖርም። ይህ በመልካም ፈቃደኝነት የሚመሰረት አጋርነት በትብብር ስራወችን ለመተግበር የሚያስችል ሲሆን የትኛውንም አካል የሚያስገድድ አይደለም። ማንኛውም አላማችን የሚደግፍና ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ና የፖለቲካ ድርጅት ያልሆነ ተቋም ወይም ቡድን በየትኛውም የአለም ዳርቻ የንሥር ብሮድካስት አጋር መሆን ይችላል። ንሥር ብሮድካስት ከፖለቲካ ድርጅት ጋር አጋር መሆን አይችልም። ንሥር ብሮድካስት ስምምነቱን ከተቀበለው የድርጅተወን ሎጎ/አርማ ከአጋር ድርጅቶቹ ዝርዝር ውስጥ በማካተት አርማወትን በድህረገፁ ላይ ያሰፍራል፤ ያስተዋውቃል። በማንኛውም ጊዜ የሚዲያ ሽፋን ሲያስፈልገወ ቅድሚያ በመስጠት ይተባበራል። ድርጅተወ እንዲጎለብት በማስተዋወቅ እገዛ ሊያደርግ ይችላል። ስምምነቱ በአመት አንድ ጊዜ ሊታደስ ይችላል። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም አጋር ድርጅቱ ስምምነቱን ሳይገደድ ማቋረጥ ይችላል። ንሥር ብሮድካስትም በተመሳሳይ ስምምነቱ አስፈላጊ ሆኖ ካላገኘው በማንኛውም ጊዜ አጋርነቱን በመልካም ሊያቋርጥ ይችላል። የአጋርነት ስምምነቱ ነፃና በፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ትብብር ይሆናል። ከንሥር ብሮድካስት ጋር በአጋርነት ለመስራት ፈቃደኛ ስለሆኑም እናመሰግናለን።