
አገር አቀፍ የአማራ ወጣቶች ማኅበር (አወማ) ሪፎርም በመስራት አዳዲስ ስራ አስፈፃሚዎችን መምረጡን አስታወቀ
********ከአማራ ወጣቶች ማኅበር (አወማ)***********
የአማራ ወጣቶች ማህበር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለአማራ ህዝብ በርካታ አበረታችና ጉልህ ተግባራትን አከናውኗል ።የአማራ ወጣቶች ማህበር ወቅቱ በሚፈልገው እና በሚያስተናግድበት አውድ የአማራን ህዝብ ብሎም ወጣት <በአማራነቱ> ተደራጅቶ ያለውን ማህበራዊ ፣ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቻችን እና ፍላጎታችን ለማስከበር የተቋቋመ የአማራ ህዝብ ተቋም ነው ።
በተለይም የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ወጣቱ በአማራነቱ ተደራጅቶ የአማራ ህዝብ በሚያደረገው እጅግ ፍትሃዊ ፣ህጋዊ እና ተፈጥሯዊ የህልውና ትግል ላለፉት ጥቂት አመታት የበኩሉን አበርክቶ አድርጓል ። የቅርብ ጊዜውን እንኳን ለማስታወስ ያህል ፦አሸባሪው ትህነግ ሀይል የአማራን ህዝብ ለማዋረድና አንገት ለማስደፋት ባደረገው ሶስት ዙር ወረራ በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የአማራ ወጣቶችን በተለያዩ አደረጃጀቶች ማለትም በፋኖ ፣በልዩ ሀይል ፣በሚሊሻ እና በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በመግባት የመጣውን ወራሪ ሀይል ለመመከት በታሪክ ዘንድ ከፍ ብሎ የሚነገር ታላቅ ተጋድሎ አድርጓል ።
ነገር ግን ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ አልነበሩም ።ምክንያቱም ትክክለኛ የሆነ ፣የአማራ ህዝብ ብሎም ወጣት መሰረታዊ ጥያቄዎች ፊት ለፊት ፣ ወጥ በሆነ ሁኔታ የሚያነሳ የአማራ አደረጃጀትም ይሁን ግለሰብ በመንግስታዊ ሰርዓቱ አይፈልግም ፤አይፈቅድም ።አማራ አማራ ነኝ ሲል ብርድ ብርድ ይለዋል ።የአማራ ጠሉ ሀይል (የፌደራሊስት ሀይሎች) በሙሉ <ለአማራ ብሄርተኝነት አያምርበትም እያሉ ይሳለቃሉ>።
አማራ <አማራ ነኝ!!> ብሎ መቆም ሲጀምር ታንኩም ፥ባንኩም ከያዘው መንግሰታዊ ስርዐት ጀምሮ ፤ተደማሪ ፣ተደጋፊው እንዲሁም አማራን በጠላትነት የፈረጀው ጎራ ( Anti-Amhara Establishment) በሙሉ መንጫጫት ይጀምራል ።የአማራ የተባሉ አደረጃጀቶችን ፣የአደረጃጀት መሪዎችን ከቻሉ ለማጥፋት ፣ካልሆነ ግን የእነሱ ምስለኔ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል ፣እያደረጉም ይገኛሉ ።
የአማራ ወጣቶች ማህበርም የዚህ ጎራ (Anti-Amhara Establishment ) ፤በከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀሰው ትክክለኛ የአማራ አደረጃጀት እና መሪዎች እንዳይኖር የሚሰራው የውስጥም ፥የውጭም የአማራ ጠላቶች ሰለባ ነበርን ።በመሆኑም በተመሰረተበት ወቅት በነበረው አማራዊ ወኔ ፣እልህ ፣ቁጭት እንዲሁም ለአማራ ህዝብ ዋስትና ፣መስዕዋት ለመሆን የነበረን ጉጉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቀዛቅዟል ።ይሁንና በተወሰኑ የዞን ከተሞች ፣ወረዳዎች ከበርካታ መንግስታዊ አፈና ፣ፈተናዎች እንዲሁም ዋና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን በጥቅም የመደለልና የማስኮብለል አጣብቂኝ ውሰጥ ሆነን ፈተናዎችን በመጋፈጥ አወማ የተቋቋመለትን ዓለማ እያከናወነ እስከ አሁኑ ጊዜ ደርሰናል ።
የአማራ ወጣቶች ማህበር ከዚህ ቀደም የነበሩበትን ደካማና ጠንካራ ጎኖቹን ነቅሶ በማውጣትና በመገምገም ደካማ የሆንባቸው አርመን ፤ጠንካራ የነበሩትን ደግሞ ለማስቀጠል አፈር ልሰን ፤እንደ ንስር ታድሰን በአዲስ መንፈስ ፣በአዲስ ዕውቀት ፣በአዲስ ሀይልና ጉልበት ዳግም ተነስተናል ።
በአሁኑ ወቅትም ማህበሩ በአዲስ ሁኔታ ራሱን አጠናክሮ ከዛሬ ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ፤ወቅቱን በሚመጥን እና በተሻለ ሁኔታ የአማራ ህዝብ አለኝታ የሆነ ተቋም በመሆን አዳዲስ ስራ አስፈፃሚዎችን መርጧል ።በዚህ መሰረት የአገር አቀፍ የአማራ ወጣቶች ማህበር ዘጠኝ(9) ዋና ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ሶስት(3) የኦዲት እና ቁጥጥር አባላትን በመምረጥ ሪፎርማችን አጠናቀናል ።
ዘጠኙ ስራ አስፈፃሚዎች የሚከተሉት ናቸው ፦
1).ሰብሳቢ –ኃይለሚካኤል ባየህ
2).ም/ሰብሳቢ–ሰሎሞን ሙላት
3).ፀሐፊ–ብሩክ ስለሽ
4).ገንዘብ ያዥ –ፈንታሁን ጓዱ
5).ሂሳብ ሹም– ቴዎድሮስ ተፈራ
6).የህዝብ ግንኙነት– አዶናይ አበበ
7).የአባላትና አደረጃጀት –ሰለሞን ልመንህ
8).የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ–ይትባረክ አባይ
9).የሴቶች ዘርፍ –ይታገሱ ስጦታው ናቸው ።
የኦዲትና ምርመራ አባላት ደግሞ ፦
1).አረጋ አባተ
2).ሽታሁን ዘመናይ
3).ንጉስ አበበ ናቸው ።
ዳግም ላንሰበር ፣ላንዋረድ በአማራዊ ወኔ ፣ንቃት እና ብቃት የህዝባችንን ህልውና ለማስከበር ዳግም ተነስተናል ።በአማራ ወጣቶች ተጋድሎ የአማራን ህዝብ ህልውና ፣ክብር እና ልዕልና እናስከብራለን ።
የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ)
ጥር 3/2015 ዓ.ም
አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል‼️
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።

