
ንሥር ብሮድካስት
ታህሳስ 21/2015
አማራ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት ከ500 ሺህ በላይ ደንበኞችን በማፍራት 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ላይ ከ531 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዘገቡን አስታወቋል
አማራ ባንክ ለዘርፉ ፋና ወጊ ተሞክሮ እያበረከተ እንደሆን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታ ተናገሩ፡፡
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የመጀመሪያ የሆነውን የባለ አክሲዮኖች አንደኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።
ጉባዔውን ያስጀመሩት የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታ በወጀብ ዉስጥ ሆኖ የባንክ ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው አማራ ባንክ ምስረታ ካደረገበት ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ፋና ወጊ ተሞክሮ እያበረከተ እንደኾነ ገልጸዋል።
ባንኩ ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 30/2022 እ.ኤ.አ በ11 ቀናት አፈጻጸም :-
75 ቅርንጫፎች 401 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ከ 82 ሺህ አስቀማጮች 237 ሚሊዮን ብር ትርፍ ከታክስ በፊት አስመዝግቧል፡፡ እስከ አሁን ባለው ደግሞ፡ 201 ቅርንጫፎች 3 ሺህ 547 ሠራተኞች 500 ሺህ 50 ደንበኞች 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተቀማ
*6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር ሰጥቷል። 531 ሚሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ አቶ መላኩ ባንኩ ወደፊት አቅሙን የበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት። ጠቅላላ ጉባዔውም የቀጣይ ጉዞዉን ቀናኢ ለማድረግ እንደሚጠቅመው ገልጸዉ ለባንኩ መልካም አፈጻጸም አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል ። የሰው ኀይልን ጥራት እና መጠን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ፋይናንስ አቅምን ማሳደግ፣ የደንበኛን ቁጥር ማሳደግ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ተብሏል።
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።