
ንሥር ብሮድካስት
ታህሳስ 20/2015
የፈደራል መንግሥቱ ሠራዊት መቀለን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ወደ ትግራይ መልሶ ጀምሯል። ረቡዕ ታኅሣሥ 19/2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው የተጓዦች አውሮፕላን በትግራይ መዲና መቀለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ መድረሱ ተዘግቧል። አየር መንገዱ ወደ መቀለ በረራ እንደሚጀምር ከተገለጸ በኋላ ወደ ትግራይ መጓዝ በሚፈልጉ ሰዎች የአየር መንገዱ ቲኬት ቢሮዎችን ተጨናንቀው ነበር ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://buff.ly/3NFvWam
FaceBook:https://buff.ly/3UxZqJq
Telegram:https://buff.ly/3Tcx06A Website: https://buff.ly/3DETCqV
Twitter:https://buff.ly/3E6WI8x
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
