
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት በአማራ ላይ የለየለት የዘር ፍጅት እየተፈጸመ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ይህንን የጅምላ ፍጅት የሚያስቆም እና በቡድን መሳሪያ ታግዘው የሚጨፈጭፉ ኦነጋዊያንን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ አካል አልተገኘም።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት ስምሪት የሚሰጠው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኮማንዶ እና የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጥምር ሀይል በጋራ በመቀናጀት በወለጋ አሁንም በማንነታቸው ብቻ ለይተው አማራዎችን በተደጋጋሚ እያጠቁ መሆናቸውን ታማኝ ምንጮች ዘግበዋል።
ከሰሞኑ በተሰነዘረው ጥቃትም ከ60 በላይ አማራዎች ተገለዋል። በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
