
ለሚመለከተው ሁሉ
የአማራ ህዝብ የዘር ፍጂት ተባብሶ መቀጠሉ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ወደ ለየለት ምስቅልቅል የሚወስዳት ማሳያወች በተረኛው አገዛዝ እንደቀጠለ ነው ።በመሆኑም ሁሉም ኢትዩጲያዊ ትኩርት ሊሰጠው ይገባል። የአማራ ህዝብ ኢትዮጲያ በሚላት ሃገሩ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ በተጠና መልኩ እየተሳደደ እየተገደለ አገዳደሉም ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ መልኩ የዘር ፍጂት እየደረሰበት መሆኑን በአደባባይ ሁሉም እያየው ነው ።በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊሰማው ይገባል:: እኛም የተሴረብንን የመጥፋት አደጋ ቀልብሰን የሰሩትን ግፍ በጥቁር መዝገብ እናሰፈራለን! በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀረምና !
የሚከተሉት ነጥቦች በአሰቸኳይ እንዲቆሙ እናሳስባለን
1, አዲስ አበባ ከፍ ሲል የአፍሪካ መዲና ሲቀጥል የኢትዩጵያን ዋና ከተማ ናት። የአንድ መንደር ከተማ ለማድረግ በተጠና መልኩ የሚደርግ እንቅስቃሴ እንዲቆም!
2,የታፈኑ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጋዜጠኞች የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባሎች ጀግና ፋኖወች ከሚደረስባቸው አሰቃቂ ድብደባ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆምና እንዲፈቱ ;
3,የኦሮሚያ ባንዲራ ከአዲስ አበባ እንዲወረድ; አዲስ አበባ የኦሮሚያ ሳትሆን የሁሉም ክልሎች መናገሻ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት:: ስለሆነም ውስጥ ለውስጥ የሚሰራው ደባ እንዲቆም! የታፈኑ መምህራን እና ተማሪወችም ከእስር ከድብደባ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ!
4 በወለጋ የሚደረገው አማራን የማፅዳት ዘመቻ ዘግናኝ ግድያ ሸሽተው ነብሳቸውን እንዳያድኑ እንዲሁም በተጠለሉበት ሳይቀረ ኦነግ ሸኔ በተባለ የዳቦ ስም የኦሮሚያ ልዩሃይል እና በተለያየ የመንግስት መዋቅር የተሰገሰጉ ከላይ እስከታች ያሉ ፅንፈኞች ስውር ደባ አማራ የሆነን የማፈን እና እረብጣ ብር ማስከፈል ይቁም ።
5 ለአማራ ህዝብ ድምፅ የሚሆኑ የነቁ ጀግኖችን በማፈን ማሰር እና ስውር ቦታ ወስዶ መደብደብ እንዲቆም እየጠየቅን ከላይ ያስቀመጥናቸው ነጥቦች እንዲተገበሩ ህዝቡ የድረሻውን እንዲወጣ እናሳስ ባለን::
መንግስት ነኝ የሚለው አካል እንደማይፈታው ብናምንም እንደማያዋጣ እና እንደማይሳካ ለማሳወቅ እንወዳለን።ይህ ካልሆነ አንድ አማራ ፋኖ የትግል አቅጣጫ አብረን የምናየው ይሆናል።
ማሳሰቢያ
-ለአማራ ህዝብ
የተደረገብህን የዘር መጥፋት ለመመከት በምናደረገው ትግል ከፋኖ ጎን እንድትቆም!
-ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ;
የአማራ ህዝብ የታወጀበትን የመጥፋት አደጋ ለመከላከል በምናደረገው ትግል ከጎናችን እንድትቆሙ እናሳስባለን
-ለኢትዩጲያ መከላከያ ሰራዊት
-ለአማራ ልዩ ሃይል
-ለክልሎች የፅጥታ ሃይሎች ለፓረቲ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የቆማችሁ ጀግኖች በሙሉ
ሀገራችን እየደረሰባት ያለውን ደባ ተረድታችሁ ለእውነት እንድትቆሙ እንጠይቃለን ።
/ለአንድ አላማ አንድ መሆን /
አንድ አማራ ፋኖ
ድል ለፋኖ
ድል ለኢትዮጵያውያ

