
ታህሳስ 14/2015
በዛሬው ዕለት ታህሳስ 14/2015/ዓ.ም ከባድየገለፁት ውጊያ እንደከፈተባቸው የገለፁት የንሥር ብሮድካስት ምንጮች የአማራ ህዝብ ሀሮ አዲስ አለም ቀበሌ ላይ በኦሮሚያ ልዩ ሀይል እና በኦነግ ሸኔ ጥምር ጦር እየተጨፈጨፈ ነው ሲሉ በስልክ ገልፀውልናል።
የምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ የሐሮ አድስ አለም ቀበሌ አማራዎች እንዳሉት በዛሬው እለት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከኪረሙ ከተማ በተነሱ የኦሮሚያ ልዩ ሐይሎች፣ በኦሮሞ ሚኒሻዎች፣ ፖሊሶች እና በሽምቅ ተዋጊ ሐይሎች ጥቃት ተሰንዝሮብናል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በሐሮ አድስ አለም የከተማዋ ዳር ዳር ውጊያው እንደቀጠለ ነው የሚሉት የችግሩ ሰለባዎች በዛሬው ጥቃት ህፃናት ሴቶች እና አቅመ ደካሞችም መገደላቸውን ተመልክተናለ ሲሉ የችግሩ ሰለባዎች ለንሥር ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በወለጋ ኪረሙ ወረዳ ከባድ ጥቃት ስለተከፈተ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሐሮ አድስ አለም ቀበሌ እንዲገባ እና ለህይወታቸው እንድደርስላቸው የችግሩ ሰለባዎች ጠይቀዋል።
=====================
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ ንሥር ብሮድካስት ብለው በ “0588380043” ይደውሉ!!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://buff.ly/3NFvWam
FaceBook:https://buff.ly/3UxZqJq
Telegram:https://buff.ly/3Tcx06A Website: https://buff.ly/3DETCqV
Twitter:https://buff.ly/3E6WI8x
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
