

በአዲስ አበባ ንፍስ ስልክ ክፍለ ከተማ የነበረው በአሁኑ ኦሮሞያ የተከለለ ሲሆን በተለምዶ ሀጫሉ መንገድ ወይንም ተክለ ሀይማኖት ይባላል:: እናም ዛሬ ጠዋት በቀን 13/04/2015 ዓ ም መሳሪያ አላችሁ በማለት የአማራ ተወላጆች ላይ ተመርጦ አፍና እየተካሄደ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪወች አሁን አሳውቀዋል::
በተጨማሪ በአዲስ አበባ ንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ ናይል ማደያ አካባቢ በቀን 08/04/2015 ዓ ም ብዙ የአማራ ተወላጆችን ፍኖ ናችሁ በሚል ታፍነዋል ብለዋል የአካባቢው ነዋሪወች:: ከታፈኑት መካከል አንዳንዶች የተለቀቁ ሲሆን ሌሎችን የት እንዳደረሷቸው አይተወቅም ብለዋል:: ሸጋው ታደለ; ይበልጣል ቢያዝን; ደረጀ ሳህሌ ታፍነው ቆይተው የተለቀቁ ሲሆን ሙሉሰው አታላይንና መኩን ጨምሮ ሌሎች የት እንዳደረሱአቸው አይታወቅም ብለዋል:: ብዙ መምሪያዎችና ፓሊስ ጣባያ እስከ ፔፕሲ ቂልንጦ ድረስ ጠይቀናል የለም የሚል ምላሽ ነው የሰጡን ሲሉ የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል::
አዲስ አበባ የማን ናት? የአዲስ አበባን ወጣት ፋኖ ነው በሚል ግራ የገባው መንግስት የጀመረውን ወከባ በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል::
===========================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting