
13 የኦሮሞ ተወላጆች የብሔራዊ ደህንነት አባላት መንግስትን ከድተው መሰወራቸው ተሰምቷል። እንደምንጮች ገለፃ አሁን ላይ በርካታ የደህንነት ሰዎች የሽብር ቡድን የሆነውን ኦነግ ሸኔን በመቀላቀል ላይ ናቸው ብለዋል።
የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና ኦነግ ሸኔ የአንድ ሳንቲም ሁለትገፅታዎች ናቸው የሚሉት ምንጫችን አባትና ልጅን ጨምሮ ቁጥራቸው 13 የሚደርሱ የመንግስት የደህንነት አባል የሆኑ አካላት ኦነግ ሸኔ የተባለውን ቡድን ተቀላቅለዋል ብለዋል።
በአጠቃላይ በአመራር ደረጃ የነበሩትን ጨምሮ ብዛታቸው 13 የሆኑ የኦሮሞ ተወላጅ የደህንነት መስሪያ ቤቱ አባላት ተቋሙን ከድተው የሽብር ቡድኑን መቀላቀላቸው ተነግሯል፡፡
ከነዚህ ሰዎች መካከል 7ቱ በእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ስር ለብዙ አመታት ከፍተኛ ስልጠናና ትምህርት በመንግስት ከፍተኛ ወጪ የወሰዱ ናቸው ተብሏል።
ቀሪዎቹ በሀገር ውስጥ ስልጠናቸውን አጠናቀው በቅርቡ ጊዜ መስሪያ ቤቱን ተቀላቅለው የነበረ መሆናቸው ተጠቁሟል።
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
