
የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ዜጎች የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችን ከመንግስት ተቋማት ማግኘት ፈተና እንደሆነባቸውም ተቋሙ ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ሰጥተውታል በተባለው ቃል መሰረት እንደ አጠቃላይ እንደ ሀገር የመልካም አስተዳደር ችግሩ እየሰፋ መምጣቱን ገልፀው ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከመንግስት ተቋማት በተገቢው መንገድ እያገኙ እንዳልሆነ ይፋ አድርገዋል።
ይህ ችግር ለዜጎች ሰፋ ያለ አገልግሎቶችን መስጠት በሚጠበቅባቸው የመንግስት ተቋማት የሚብስ ሲሆን ከተማ አስተዳደር፣ ወረዳ እና ቀበሌዎች ዋና ተጠቃሾች መሆናቸው ተገልጿል።
=====================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።
