
ኦነግ ሸኔ በአዲስ ዘመቻ በደራ አማሮችን እየገደለ እና እየዘረፈ መሆኑ ተሰማ
ሰኔ 26/2014 ዓ.ም
ንሥር ብሮድካስት
ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እያደረሰ ባለው ጥቃት አማሮች ተለይተው እየተገደሉ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ደራ ወረዳ በከባድ መሣሪያ እየተደበደበች ሲሆን፣ ባቡ ድሬ፣ አሙማ ግንደ ፣ እሮብ ገበያ ፣ ግንደ በርበሬ ቀበሌዎች ያሉ አማሮች እየተገደሉ እና እየተሰደዱ ናቸው።
በጥቃቱ በተለይ ሴቶች፤ ሕጻናትና አዛውንቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአማራ ገበሬ እንስሳትም ተዘርፈዋል ።
እንደሚታወሰው፣ ከጉንደ መስቀል ደራ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 260 ተሳፋሪዎች በኦነግ/ሸኔ ታግተው ነበር። ከእነዚህ መካከል ስምንት አማሮች ተለይተው እስካሁን ድረስ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ አይታወቅም ሲል ባልደራስ አስታውቋል።
ንሥር ብሮድካስት
ሰ.አሜሪካ
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት ፡
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
Tiktok https://vm.tiktok.com/ZTds2F1e9
www.nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።