
በቃ!
========ከንሥር እንግዳ=========
የምትጠሉትንና የምትንቁትን ህዝብ ማስተዳደር አትችሉም።
በየቀኑ በጥይት አረር ያስጨፋጨፋችሁትን ህዝብ ወኪልህ ነን ልትሉት አይገባም።
ተከባብሮ መኖር #ንቀትን እና ምን ታመጣላችሁ እያሉ መደብደብ ፣ሰላም መንሳት እና ማህበራዊ ወረትን መቀማት ይብቃ!!
አማራ ሃገሩን የሚወድ ህዝብ እንጅ በፍርሃት ሰቀቀን ውስጥ አስገብተህ በአረመኔዎች የምታስጨፈጭፈው ህዝብ አይደለም።
ሁሉን የሚችል፣የሚያስብ እና የሚያሰላስልን ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንድፈፀምበት አንፈቅድም!!
ትላንት ዛሬ አይደለም።ማህበረሰባችን ሁሉ ነገር ገብቶታል።የአማራን ሞት ሁሉም በተግባር እና በመዋቅር የሚፈፅሙት እንጅ በደንገት የሚከሰት ድርጊት አለመሆኑን አስተውለናል።
ለብዙ ዘመናት ለሃገረ መንግስቱ ደጀን ከመሆን ውጭ ሌላ ነገር አላደረግንም።
መንግስት ብዙ ነገሩን ይረዳል ብለን ብናስብም በህልውናችን ላይ ድርብርብ ችግሮችን ፈጥሯል።
ከህወሓት ወረራ እስከ ሸኔ የወለጋው ጭፍጨፋ ድረስ የመንግስት የባከነና ያረፈደ ውሳኔ በህዝባችን ላይ ተስፋ አሳጥቶናል።
ስለሆነም ወጣት ሆይ ይህን አሮጌ መዋቅራዊ አስተዳደር ከትከሻህ ላይ አውርድ።ነፃነት በተራ ንትርክ የሚመጣ አለመሆኑን ብዙ የታሪክ ድርሳናትን ማገላበጥ አያስፈልግም።ትላንት ወያኔን በስንት ጀግኖች የደም ዋጋ ከአራት ኪሎ አሺቀንጥረን መጣላችን ይታወሳል።
ስለሆነም ትግላችን ፈታኝ ቢሆንም የመዳረሻ ግባችን ግን አማራ እና አማራዊያንን መመስረት ነው።
የአማራ ህዝብን በመስዋአትነት እየበላች የምትኖር ሃገር ጋር የለችንም።
በደማችን ያፀናናትን ሃገር ወንበደዎች እያፈረሷት ነው።
በፈረሰች ሃገር ላይ ያለ ምክንያት መታገል ለወጥ አያመጣም። ትግላችን ከወንበደዎች እና ከሃገር አፍራሾች ጋር ነው።
አማራን እየገደሉ #ኢትዮጲያዊ ነኝ ማለት ዘመኑ ያለፈበት ፋሺን ነው።
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ከንሥር እንግዳ
እውነት ነው::