
አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ አላማ እና የተለያዬ ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ሾፌሮች በኦሮሚያ ክልል መንግስት እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ::
ንሥር ብሮድካስት ግንቦት 8/ 2014 ዓ.ም
ከደብረ ብርሃን ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በተለምዶ ኦባማ የሚባለውን ተሽከርካሪ ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ሁለት አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ዞን ለገጣፎ ለገዳዲ ሚሽን በሚባል አካባቢ እንደታሰሩ ተገልጧል።
ሾፌሮቹ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ አላማ፣ የሻለቃ መሳፍንት እና የጄኔራል አሳምነው ጽጌ ምስል ያለበት ቲሸርት ለብሰዋል በሚል ያለ ጥፋታቸው መታሰራቸውን የተናገሩት ቤተሰቦች መኪናቸው ጭምር የተያዘ መሆኑን ጠቁመዋል። በግፍ የታሰሩትም:_ አሌክስ ደርቤ እና ባሳዝን ደርቤ የተባሉ የደብረ ብርሃን ልጆች ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪም ሌሎች የአማራ ወጣቶችም እየታሰሩ መሆኑን አሚማ ዘግቧል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ጣልቃ በመግባት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን በተለይም በትምህርት ተቋማት ያሉትን በኃይል በማስወረድ በኦሮሚያ ባንዲራ የመተካት ስራ እየሰራ ነው፤ ክልላዊ መዝሙር እንዲዘመር እያደረገ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እየተነሳበት ነው።